መቅረዝ መረዳጃ እድር

አብሮነት ለተሻለ ማህበራዊ ህይወት

📢 ማሳሰቢያ፡ የመጋቢት ወር መዋጮ በጠቅላላ ጉባዔ ውሳኔ መሠረት 500 ብር መሆኑን እንዳይረሱ። --- 💰 የወርሃዊ ክፍያ ወር በገባ እስከ 10ኛው ቀን መሆኑንም እንዳይዘነጉ ።

ትኩስ ዜናዎች

የመቅረዝ እድር ዲጂታል አገልግሎት በይፋ ተጀመረ

ዛሬ መጋቢት 11 ቀን 2018 ዓ.ም እድራችን ዘመናዊ የዲጂታል አሰራርን በይፋ ስራ ላይ መዋሉን ለተከበሩ አባላቶቻችን በደስታ እንገልጻለን።

ደረጃ 1፡ የመተዳደሪያ ደንብ አጭር መግለጫ

1. መግቢያ እና ዓላማ

እድሩ በበኣታ ለማርያም እና በግቢ ገብርኤል አካባቢ አብሮ አደግ በሆኑ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ልጆች ህዳር 8 ቀን 2017 ዓ.ም ተመሠረተ። ዋና ዓላማው በአባላት መካከል ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ትስስርን ማጠናከር፣ በሀዘንና በደስታ ጊዜ መረዳዳት፣ እንዲሁም በበጎ አድራጎት ስራዎች መሰማራት ነው።

2. የአባልነት መስፈርቶች፣ መብቶች እና ግዴታዎች

  • መስፈርት፦ የኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነት ተከታይ፣ ዕድሜው ከ18 ዓመት በላይ የሆነ እና በ3 አባላት ምስክርነት የቀረበ።
  • ቤተሰብ፦ የአባሉ ባለቤት፣ ልጆች፣ ወላጆች እና የስጋ እህት/ወንድሞች እንደ ቤተሰብ ይመዘገባሉ።
  • መብትና ግዴታ፦ አባላት የመምረጥና የመመረጥ፣ በእክል ጊዜ ድጋፍ የማግኘት እና ንብረት የመጠቀም መብት አላቸው።
  • የመመዝገቢያ ክፍያ፦ ማንኛውም አዲስ አባል ሲመዘገብ 3,000 (ሦስት ሺህ) ብር መክፈል ይኖርበታል።
  • ወርሃዊ ክፍያ፦ ማንኛውም አባል 500 (አምስት መቶ) ብር ወርሃዊ መዋጮ የመክፈል ግዴታ አለበት።

3. የአደረጃጀት መዋቅር

ጠቅላላ ጉባኤ፦ የእድሩ የበላይ አካል ሲሆን በዓመት ሁለት ጊዜ (ጥር እና ሐምሌ) ይሰበሰባል።
ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ፦ በጉባኤ የሚመረጡ 7 አባላት ያሉት ሲሆን የአገልግሎት ዘመናቸው 3 ዓመት ነው።
ኦዲተር፦ የፋይናንስ እንቅስቃሴን ይቆጣጠራል።

4. የሚሰጡ አገልግሎቶች

አጭር ጊዜ (ከ1 ዓመት በኋላ)፦ በህመም፣ በደስታ (ጋብቻ) እና በሀዘን ወቅት የገንዘብና የማህበራዊ ድጋፍ ማድረግ።
ረጅም ጊዜ (ከ2 ዓመት በኋላ)፦ አዋጭ የኢኮኖሚ ዘርፎች ላይ መሰማራት፣ የአባላትን ጤና መደገፍ እና አቅመ ደካሞችን መርዳት።

5. የዲሲፕሊን ስርዓት

ማንኛውም ውሳኔ በድምፅ ብልጫ ይተላለፋል። አንድ አባል ያለ በቂ ምክንያት በስብሰባ ካልተገኘ ወይም ግዴታውን ካልተወጣ ይቀጣል። የእድር ንብረትን ለሶስተኛ ወገን አሳልፎ መስጠት ከአባልነት ያሰርዛል።

መቅረዝ መረዳጃ እድር

የአባልና የቤተሰብ ቅፅ

እንኳን ደህና መጡ፣ አቶ ወንድማገኝ

ጠቅላላ የከፈሉት፡ 2,400 ብር

🛠 የአስተዳዳሪ መቆጣጠሪያ (Dashboard)

120

ጠቅላላ አባላት

1

የሚጠባበቁ ማመልከቻዎች

5,400 ETB

የዚህ ወር ገቢ

📩 አዲስ የመጡ ማመልከቻዎች

የአመልካች ስም ስልክ ቁጥር ቀን ውሳኔ
አቶ አበበ ባልቻ 0912345678 12/05/2026

👥 የአባላት ዝርዝር